#Ethiopia | የአለም ጤና ድርጅት ሊቀመነበር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያውያን የሚገባቸው ሰላም እንጂ ጦርነት አይደለም አሉ።
ለኢትዮጵያዊያን በዚህ ሰአት ልማትና አብሮነት እንጂ ተጨማሪ ጦርነትና ውድመት እንዳልሆነ በመጠቆም ባለድርሻ አካላት ሁሉ ከጠመንጃ ይልቅ ሰላማዊ ንግግርን እንዲመርጡ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣው የኃይል ግጭት ከፍተኛ የሰው ሕይወት መጥፋትን መፈናቀልንና ማህበራዊ ውድመትን እያስከተለ በመሆኑ ሁሉም አካላት የጦር መሣሪያን በመተው ወደ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በአሁኑ ወቅት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በአፋር እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚታዩት የትጥቅ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወት በጽኑ እየፈተኑ ይገኛሉ።
ለዓመታት የቀጠለው ይህ ግጭት ዘላቂ መፍትሔ ያላመጣ ሲሆን ይልቁንም የህዝቡን እንግልት እና የኢኮኖሚ ውድቀት እያፋጠነው መሆኑ አመላክተዋል
የጦርነቱ ቀጥተኛ ሰለባ የሆኑት ንጹሐን ዜጎች ሲሆኑ የጤና የትምህርት እና የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች መቋረጣቸው የዜጎችን ሕይወት የበለጠ አሰቃቂ አድርጎታል።
የትጥቅ ፍልሚያ የህዝቡን ብሶትና ቅሬታ ከመጨመር ባለፈ ለተወሳሰቡ የፖለቲካ ጥያቄዎች መፍትሔ ማምጣት አለመቻሉም ገልጸዋል።
የፌደራል መንግሥት የክልል አመራሮችና የታጠቁ ቡድኖች የሕዝቡን ስቃይ በማስቀደም በጠረጴዛ ዙሪያ በመቀመጥ ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Ethiopia #peace #war
#WHO #tewodrosadhanom
Source: GetuTemesgen









No comments yet.