#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው ‘ትሩዝ ሶሻል’ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋር የሚያነጻፅራቸውን የፈረስ ሐውልቶች ምስል አጋርተዋል።
በምስሉ ላይ በኦባማ ስም የተሰየመው ሐውልት ያረጀና የጠቆረ ሆኖ ሲታይ በትራምፕ ስም የቀረበው ደግሞ በወርቅ ቀለም ያበራ ሆኖ ተስሏል።
ትራምፕ ከምስሉ ጋር ምንም ዓይነት ተጨማሪ መግለጫ ያላስቀመጡ ሲሆን ይህ አጋጣሚ የራሳቸውን የሥልጣን ዘመን ከቀደሙት ፕሬዝዳንቶች ጋር በማህበራዊ ሚዲያ የማነጻጸር ልማዳቸውን የቀጠሉበት ሌላኛው ማንጸሪያ ሆኗል።
ሰውየው ባራክ በአሜሪካውያን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው በህይወት ያሉ የቀድሞው ፕሬዝዳንት መሆናቸው ሰላም እንደሚነሳቸው አልሸሸጉም።
ስለሆነም ትራምፕ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቀድሞውን ፕሬዚዳንት የሚያኮስሱ ልዩ ልዩ ተግባራት ለመፈጸም ሲጥሩ ይስተዋላል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.