የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕለተ ሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ “መሐለ እግዚአብሔር ለዳዊት…” በሚለው ውስጥ የሚነሳ ታሪክ እናገኛለን፡፡
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በንግስናው ዘመን በጊዜው የነበረው ነቢዩ ቅዱስ ናታን ወደ ቤተ መንግስቱ ሊጠይቀው ሲመጣ ንጉሱን አዝኖ ተክዞ አየው፡፡ “ምነው አዝነሀል ተክዘሃል?” አለው፡፡ እርሱም “እኔ በጽድ በዝግባ ከተሰራ ቤተ መንግስት ተቀምጬ፣ ታቦተ ጽዮን በድንኳን ተቀምጣ ምነው አላዝን አልተክዝ?” አለው፡፡
ነቢዩም መልሶ “ጠላት እንደሆነ ጠፍቶልሀል፣ ለምን አታንጽም?” አለው፡፡ ቅዱስ ዳዊትም “ያስ ቢሆን ለእግዚአብሔር ካላመለከትክልኝ ይሆናልን?” አለው፡፡ ሁለቱም ሱባኤ ሲገቡ ለነቢዩ ቅዱስ ናታን “አኮ አንተ ዘትነድቅ ሊተ ቤተ፣ አላ ወልድከ ዘወጽአ እምሐቔከ” “አንተ አይደለህም ቤቴን የምትገነባው፣ ከአብራክህ የወጣው ልጅህ እንጂ” ብለህ ንገረው የሚል መልዕክት ከእግዚአብሔር ተነገረው፡፡
እንደተባለውም ጠቢቡ ንጉስ ሰሎሞን አሁን ድረስ ወደር ያልተገኘለትን ቤተ መቅደስ ገነባ፡፡
እንደ ቅዱስ ዳዊት በተመቸ ቤት ብንቀመጥ እንኳ እግዚአብሔርን ብለው አለሙን ትተው እጅግ በአስቸጋሪ የአለም ፈተና ውስጥ ሆነው ስለኛ ሰላምና ድኅነት ሌት ተቀን የሚማልዱልንን ገዳማዊያንን ማስታወስ ይገባናል፡፡
እኛ በሞቀ ቤት የልብስ መዓት ደራርበን ስንተኛ “ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ፈርሶ ይገኛል፣ መነኮሳቱም በድርቅና በርሃብ ከባድ ፈተና ውስጥ ሆነው ድጋፋችንን እየጠበቁ ነውና የድጋፍ እጃችንን እንዘርጋላቸው።
በረሃብ ውስጥ መኖር የዕለት እንጀራን ብቻ ማጣት ሳይሆን ጤናን፣ ክብርንና ተስፋን የሚፈታተን አስከፊ ሕይወት ነውና ካለን ላይ በማካፈል ገዳማዊያኑን እንርዳ፣ለነፍሳችንም ስንቅን እንያዝ።
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227
አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132
ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921
Source: FastMereja









No comments yet.