ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጹ።የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ያላቸውን ስጋት ገለጹ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዛሬው ዕለት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ግጭት እንዲቆምና በአስቸኳይ ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲመጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ባሰፈሩት ጽሁፍ “ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ተጨማሪ ጦርነት አይደለም” በማለት አገሪቱ ያለችበትን አስከፊ የጸጥታ ሁኔታ አመልክተዋል። 
ዶክተር ቴዎድሮስ በዝርዝር በገለጹት ነጥብ በአማራ ክልል ለሦስት ዓመታት የዘለቀው የትጥቅ ግጭት የበርካታ ዜጎችን ሕይወት መቅጠፉን ገልጸዋል። 
በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው ደም መፋሰስ መቀጠሉን በትግራይ ክልል ዳግም ወደ ግልጽ ጦርነት የመግባት ስጋት መኖሩን እንዲሁም የአፋር እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭትና በዓመጽ ውስጥ መቆየታቸውን በአጽንኦት ጠቁመዋል።
“ኢትዮጵያውያን ከዚህ የተሻለ ሰላማዊ ሕይወት ይገባቸዋል” ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2