ግብጽም ልትቀላቀል ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ግብፅ የሳውዲ ቱርክ እና ፓኪስታንን አዲስ የመከላከያ ጥምረት 4ኛ አባል ልትሆን ነው።

በአፍሪካ አህጉር በወታደራዊ ሀይሏ ቀዳሚ የሆነችው ግብፅ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ፣ ቱርክ እና ፓኪስታን መካከል የተመሰረተውን ታሪካዊ የመከላከያ ጥምረት ለመቀላቀል ዝግጅቷን ማጠናቀቋ ተገለጸ።

ሳውዲ አረቢያ፣ ቱርክ እና ፓኪስታን በታደሰ የውጭ እና ደህንነት ፖሊሲ “የመካ የጋራ መከላከያ ስምምነት” የተሰኘ አዲስ ወታደራዊ ህብረት በይፋ መመስረታቸው ይታወቃል።

ይህ ስምምነት የኔቶ አንዱ ከተጠቃ ሁላችንም እንደተጠቃን ይቆጠራል የሚለውን የመደጋገፍ መርህ የተከተለ ነው።

ስምምነቱ የሶስቱን ሀገራት ወታደራዊ እና የደህንነት ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ነው።

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን በሰጡት መግለጫ ግብፅ የዚህ ህብረት ቀጣይ እና አራተኛ አባል ለመሆን ሂደቶችን እያጠናቀቀች ነው ብለዋል

ሚኒስትሩ አክለውም ግብፅ በሁሉም የቀጣናው ጉዳዮች ላይ ዋነኛ አጋራችን ናት ህብረቱን መቀላቀሏም የጋራ ደህንነታችንን በከፍተኛ ደረጃ ያጠናክረዋል ብለዋል።

ይህ አዲስ ጥምረት በቀጣናው እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ሊቀይር እንደሚችል የጂኦ ፖለቲካ ተንታኞች ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Nato #Egypt
#defensepact #Turkey
#pakistan #Saudi


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1