የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ 1898 ተማሪዎችን አስመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | የቀጣናውን ሀገራት የሰው ኃይል ለማብቃት ከደቡብ ሱዳንና ሶማሌላንድ የመጡ ተማሪዎችን በነፃ ትምህርት ያሰለጠነው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት፣ 1,898 እጩ ባለሙያዎችን በዛሬው እለት አስመርቋል።

‎ተቋሙ ከታዳጊነት እድሜ ጀምሮ የሚሰጠውን የክህሎት ማበልጸጊያ እና የቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታወቀ ሲሆን፣ ይህ አሰራር የአህጉሪቱን የጋራ እድገት ለመደገፍ ትልቅ እምቅ አቅም እንዳለው ተመላክቷል።

‎በምርቃት መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የስራና ክህሎት ሚኒስትር መፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደገለጹት፤ ትምህርትና ስልጠና የሀገርን እምቅ አቅም ለማውጣትና ችግርን ለመፍታት ወሳኝ ነውቴክኒክና ሙያ እውቀትን ከክህሎት በማጣመር እንዲሁም ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ በመፍጠር የሀገርን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚስችል ዘርፍ መሆኑን አመላክተዋል ።

‎ትምህርትና ስልጠና ለመጪው ጊዜ የሚያዘጋጁ የስንቅ ማዕዶች ናቸው ያሉ ሲሆን፣ ሰልጣኞች ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲጨርሱ በትኩረት መሠራቱን ተናግረዋል።

‎ላለፉት አምስት ዓመታት ስራን ክህሎትን እንዲሁም ኢንዱስትሪን መሠረት ያደረገ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ከዚህም የክህሎት ባንክ አንዱ ነው ብለዋል።

‎ዓለም አቀፍ ብቃት ያላቸውን ሰልጣኞች ማፍራት የሚያስችሉ ተጨማሪ የክህሎት ፓርኮች እና መሠረተ ልማቶች እየለሙ እንደሚገኙም ሚኒስትሯ ጨምረው ጠቅሰዋል።

‎ተመራቂዎች ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ በመግለጽ፤ በፅናት፣ በዲሲፕሊን፣ በትጋትና በሀገር ወዳድነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አስገንዝበዋል። በቀጣይም ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

‎የኢፌድሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገርን ወደ ሚገባት ከፍታ ለማድረስ ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ያስፈልጋታል፣ ይህም እውን ለማድረግ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል።

‎ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የጋራ ፕሮግራሞችን የማስተሳሰር ሥራ መሠራቱንም ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።

‎የልምድ፣ የክህሎት፣ የዕውቀት፣ የቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን እንዲሁም ከታዳጊነት ዕድሜ ጀምሮ የሙያ ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን አስታውቀዋል።

‎በተያዘው ዓመትም 11 አዳዲስና 34 ነባር ፕሮግራሞች ላይ የተለያዩ ስልጠናዎች ሲሰጡ የቆዩ ሲሆን፤ በዕለቱ 1583 በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም 315 ተማሪዎች በሁለተኛ ዲግሪ በአጠቃላይ ፤ 1898 ተማሪዎችን መመረቃቸው ተገልጿል።

‎#Ethiopia ​#TVET_Ethiopia ​#SkillsEthiopia #Graduation2026 ​#TVETGraduation
‎#IntraAfrica ​#SouthSudan​#Somaliland







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: