ኢዜማ ከሀገራዊ ምክክሩ ምን ይፈልጋል?የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት ፓርቲያቸው ወደ ሀገ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢዜማ ከሀገራዊ ምክክሩ ምን ይፈልጋል?
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) መሪ አቶ እዮብ መሳፍንት ፓርቲያቸው ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረክ የገባው ለአጭር ጊዜ የሥልጣን መጋራት ስምምነት ሳይሆን መሠረታዊና ሥርዓታዊ ለውጥ ለማምጣት ታግሎ ለመለወጥ መሆኑን አሳሰቡ።
መሪው አክለውም ኢዜማ እስከ ምክክሩ መዝጊያ ቀን ድረስ በማይበገር አቋም የዜግነት ፖለቲካን፣ የነፃና ገለልተኛ መንግሥታዊ ተቋማትን ግንባታ እንዲሁም በብቃት ላይ የተመሠረተ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት መዘርጋትን እንደ ዋና መሠረታዊ ምሰሶዎች አድርጎ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
  ትውልዱን ከግጭትና ከመከፋፈል አዙሪት ነፃ ለማውጣትና ጠንካራ ሀገራዊ ሥርዓት ለመገንባት እነዚህን መርሆዎች እውን ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት አቶ እዮብ፣ የዜጋ ክብር ፍጹምና የማይደፈር የሆነባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በጋራ እውን እስከሚደረግ ድረስ ፓርቲያቸው ያለማቋረጥ እንደሚታገል አጽንኦት ሰጥተዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: