ይህ የጋዜጠኛ ትዕግስት ታንቱ መልዕክት ነው።

- Advertisement -
Sidebar AD

​እስከዛሬ ድረስ በምናደርገው ጉዞ አብራችሁን ስለነበራችሁ ከልብ እያመሰገንን፣ ዛሬ አንድ ያልተጠበቀ አሳዛኝ ዜና እና ትልቅ ጥሪ ይዘንላችሁ ቀርበናል::

​እንደሚታወቀው ገሃድ ፖድካስት ባለፉት ወራት በማህበራዊ ጉዳዮች እና በተለያዩ ርዕሶች ላይ በርካታ ፕሮግራሞችን እያዘጋጀ አብሯችሁ የቆየ፣ እናንተም በቅርበት ስታግዙት የነበረ ቻናል ነው:: ሆኖም ግን ከመቶ ሃምሳ ሺህ (150,000) ብር በላይ ሰርቶልን የነበረው ዩቲዩብ ቻናላችን፣ የሰራነውን ብር ሳናወጣው ባልታወቀ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ተዘግቶብናል::

​ይህ አጋጣሚ ትልቅ መደናገጥ ቢሆንብንም፣ እጃችን ላይ በጣም ቆንጆ ቆንጆ ያልተሰሩ ፕሮጀክቶች እና አዳዲስ ስራዎች አሉ:: እነሱን ይዘን በአዲስ ሞራል እና በአዲስ አቅም ወደ እናንተ ለመመለስ ገሃድ ሚዲያ በሚል ቻናል ከዜሮ ጀምረናል!

ይህንን ጉዞ ስንጀምር ደግሞ ሙሉ በሙሉ እናንተን ተማምነን ነው::
​ስለዚህም “የ3 ቀን የ1,000 ሰብስክራይበር ቻሌንጅ” ይዘን ተነስተናል::
​ይህንን ፈተና በጋራ አልፈን አዳዲስ ስራዎቻችንን ለእናንተ ለማድረስ የእያንዳንዳችሁ ድጋፍ ወሳኝ ነው::

ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ሼር በማድረግ እና ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ በማገዝ አብራችሁን ሁኑ፣

ሊንኩ አስተያየት መስጫው ላይ አለ




Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2