#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ብሔራዊ አካባቢ የሚገኘውና የአገሪቱ አንጋፋ ተቋም የሆነው ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሆቴል የማፍረስ ሂደት መጀመሩን ከፎርቹን ጋዜጣ ሰምተናል።
ቀደም ብሎ ከሆቴሉ ጀርባ የሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ መፍረስ የጀመረ ሲሆን የዋናው ሕንፃ ማፍረስ ሥራም በጥቂት ቀናት ውስጥ ተጠናቆ በቅርብ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተገልጻል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሆቴሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙ ሰባት የንግድ ሱቆች አስቀድመው ተነስተዋል።
በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በ109 ክፍሎችና በ140 ሠራተኞች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ይህ ባለ አምስት ፎቅ ሕንጻ በ2002 ዓ.ም ታዋቂው ባለሃብ አቶ በላይነህ ክንዴ በ94 ሚሊዮን ብር በቢኬ ግሩፕ በኩል የገዙት ሲሆን አሁን ላይ በኢትዮጵያ ሆቴል ምትክ ዘመናዊ ሕንፃ ለመስራት አቅደዋል።
ተቋሙ ሠራተኞቹ እንደማይቀነሱና በሥሩ ባሉት 22 ኩባንያዎች ውስጥ እንደሚያዛውራቸው ቃል ገብቷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.