#Ethiopia | የዓለም አቀፉ ቦክስ ማህበር የስራ አስፈፃሚ ቦርድ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽንን ጨምሮ የስድስት ሀገራትን የአባልነት ማመልከቻ መቀበሉን ይፋ አደረገ።
በውሳኔው መሰረት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የቻድ፣ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ የሊቤሪያ፣ የኩዌት እና የየመን የቦክስ ፌዴሬሽኖች በወርልድ ቦክስ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት አዲስ የአባልነት ድጋፍ አግኝተዋል።
ይህ ውሳኔ የማህበሩን ተፅዕኖ በተለይም በአፍሪካ አህጉር ይበልጥ የሚያሰፋው ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በውድድሮች ላይ የመሳተፍ መብት ያላቸውን የፌዴሬሽኖች ቁጥር ወደ 184 አድርሶታል።
እነዚህ አዳዲስ አባላት ጥብቅ የሆነውን የመስፈርቶች ግምገማ በማለፍ አዎንታዊ ምላሽ ያገኙ ሲሆን ግልጽ የምርጫ ስርዓት፣ የዓለም አቀፍ የጸረ-ዶፒንግ ደንቦች አተገባበር እና ነጻ የክርክር መፍቻ አሰራር ማሟላታቸውን ማረጋገጥ ችለዋል።
በአሁኑ ወቅት የ (Endorsed Member) ደረጃ የተሰጣቸው እነዚህ ፌዴሬሽኖች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ የመሳተፍ መብት የሚያገኙ ቢሆንም በመጪው ህዳር በፓናማ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ድምፅ የመስጠት መብት አይኖራቸውም።
ሙሉ አባልነታቸው በዚሁ ጉባኤ ላይ በድምፅ ሲረጋገጥ ብቻ ከ2027 ጀምሮ በውሳኔ ሰጪነት መሳተፍ የሚጀምሩ ይሆናል። በሌላ በኩል ማህበሩ አስፈላጊውን መስፈርት ሳታሟላ የቀረችውን የካሜሩን አባልነት የሰረዘ ሲሆን ከስምምነት ውጪ በመሆኗ የኢኳዶርን አባልነት በጊዜያዊነት አግዷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.