የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ቡድን በዓለም ሻምፒዮና ደማቅ ድል አስመዘገበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አዲስ አበባ — በኦሪገን አሜሪካ በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን ከፍተኛ የውድድር መንፈስ በማሳየት 2 የወርቅ፣ 3 የብር እና 1 የነሐስ በድምሩ 6 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል።

በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ ውድድር የኢትዮጵያ ወጣት አትሌቶች ባስመዘገቡት የሜዳሊያ ብዛት ሀገራቸውን፦

* ከዓለም 5ኛ ደረጃ
* ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን በድል አጠናቅቀዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው የእንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ፤ ይህ የተገኘው ስኬት የወጣት አትሌቶቻችንን ብቃት፣ ጥንካሬ እና ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር በግልጽ ያሳየ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም ለዚህ ታላቅ ውጤት አስተዋጽኦ ላደረጉ አሰልጣኞች፣ የሕክምና እና የቴክኒክ አባላት፣ የአትሌቶች ቤተሰቦች እና ለመላው ስፖርት አፍቃሪ ምስጋና አቅርቧል።

ይህ የወጣት አትሌቶች ድል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የወደፊት ጉዞ ብሩህ መሆኑን ማረጋገጫ ሲሆን፣ ለቀጣዩ ትውልድ አትሌቶችም ትልቅ የብርታት ምንጭ እንደሚሆን ተገልጿል።

ለወጣት ሻምፒዮኖቻችን እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አለን!

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2