#Ethiopia | በመጪው ረቡዕ ነሐሴ 06 ቀን 2018 ዓም ከምሽቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በዋልያ መጽሐፍት መደብር ልዩ የሥነ ጽሑፍ ምሽት ተዘጋጅቷል።
በዕለቱም የደራሲ ይፍቱሥራ ምትኩ ሥራዎች በሆኑት በተለይ አሥራ አንደኛው እና ወድቆ የተገኘ ሀገር በተሰኙት ሁለት አዳዲስ መጻሕፍት ላይ ውይይትና የፊርማ ሥነ ሥርዓት ይከናወናል።
በመርሐ ግብሩ ላይ መምህር መሠረት አበጀ፣ ዶክተር ነጋ ፍቅሬ፣ ጋዜጠኛና ደራሲ ታሙሩ ከፈለኝ እንዲሁም ዶክተር ሰላም ማርቆስ ተገኝተው የውይይት ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የመጻሕፍት ግምገማውና የፊርማ ፕሮግራሙ የሚካሄደው በአራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው ኢክላስ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የዋልያ መጽሐፍት መደብር ውስጥ ነው።
#waliyabooks #yiftusiramitiku #bookreview #ethiopianliterature #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.