የዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ለአውሮፓ ትልቁ የጄት ነዳጅ አቅራቢ መሆን ቻለየናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ …

- Advertisement -
Sidebar AD
የዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ለአውሮፓ ትልቁ የጄት ነዳጅ አቅራቢ መሆን ቻለ
የናይጄሪያው አሊኮ ዳንጎቴ ማጣሪያ ፋብሪካ በሐምሌ ወር ብቻ ለአውሮፓ ከገባው አጠቃላይ የጄት ነዳጅ ውስጥ አምስተኛውን ድርሻ በመያዝ (ከ2.06 ሚሊዮን ቶን ውስጥ ከ400 ሺህ በላይ ቶን በማቅረብ) ለአሁኑ ወርም ከአሜሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ቀድሞ የአውሮፓ ትልቁ የውጭ አቅራቢ መሆን መቻሉ ተገለፀ።
ይህ አፈጻጸም የተመዘገበው በፋብሪካው ላይ በተከሰተ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የጥገና ሥራዎች ተከናውነው የነዳጅ ማጣሪያ አቅሙ ከነበረበት በቀን ከ600 ሺህ በላይ ወደ 350 ሺህ ቀንሶ በነበረበት ወቅት ጭምር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የአውሮፓ አገራት የኃይል አቅርቦታቸውን ለማብዛት ያላቸው ፍላጎት ለዚህ ስኬት መሠረት ሆኗል።
የፋብሪካው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቪድ በርድ እንዳሉት ተቋሙ የናፍጣ እና ቤንዚን ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ ጀምሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፋብሪካው በጥቅምት ወር 5 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ የአክሲዮን ሽያጭ እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: