አርሰናል አልሆነለትም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​አርሰናል በቅድመ-ውድድር ዝግጅቱ ለጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ተረቶ የኤሚሬትስ ዋንጫን አጥቷል።

በሳምንቱ አጋማሽ በደብሊን በሪያል ቤቲስ 3 ለ 1 ከተሸነፈ በኋላ በገዛ ሜዳው ኤሚሬትስ ሁለተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ዶርትሙንድ በጨዋታው መጀመሪያ በሳሙኤል ኢናሲዮ እና በ18 ዓመቱ ግሪካዊ ኮንስታንቲኖስ ካሬትሳስ ድንቅ ግቦች መሪነቱን ወስዶ የመጀመሪያውን አጋማሽ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አጠናቋል።

​በሁለተኛው አጋማሽ ኢታን ኑዋኔሪ በክርስቶስ ፆሊስ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ መረብ ላይ በማሳረፍ ለአርሰናል ተስፋ ቢመልስም ዶርትሙንድ ብዙ ሳይቆይ በጆአን ጋዱ አማካኝነት ሶስተኛ ግብ አስቆጥሯል።

አርሰናል በቪክቶር ዮከሬስ የፔናሊቲ ግብ ልዩነቱን ወደ አንድ ቢቀንስም ዶርትሙንድ እስከ ጨዋታው ፍጻሜ መሪነቱን አስጠብቆ በመውጣት ድል ተቀዳጅቷል።

​ከጨዋታው መጀመር በፊት አዲሱ ፈራሚ ብሩኖ ጊማሬሽ በኤሚሬትስ ስታዲየም ለደጋፊዎች የተዋወቀ ሲሆን መድፈኞቹ ቀጣይ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ከሴስ ፋብሪጋሱ ኮሞ ጋር ካደረጉ በኋላ በኮሚዩኒቲ ሺልድ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ይገናኛሉ።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1