ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገዩቲዩብ ቪዲዮ ፈጣሪዎች ከማስታወቂያ እና ከዩቲዩብ ፕሪሚየም (Y…

- Advertisement -
Sidebar AD
ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገ‼️
ዩቲዩብ ቪዲዮ ፈጣሪዎች ከማስታወቂያ እና ከዩቲዩብ ፕሪሚየም (YouTube Premium) ገቢ ማግኘት የሚጀምሩበትን የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም (YouTube Partner Program) የመግቢያ መስፈርት በሁለት እጥፍ ማሳደጉን አስታወቀ።
እ.ኤ.አ ከፌብሩዋሪ 1, 2027 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት፡-
📌 በመደበኛ (ረጃጅም) ቪዲዮዎች፡ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 8,000 የታዩ ሰዓታት (Watch Hours) ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። (ቀደም ሲል ከነበረው 4,000 ሰዓታት በሁለት እጥፍ ያደገ ነው)።
📌 በአጫጭር ቪዲዮዎች (Shorts)፡ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊየን እይታዎችን (Views) ማሳካት ይኖርባቸዋል። (ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ሚሊየን እይታ በሁለት እጥፍ ጨምሯል)።
📌 የተከታዮች ብዛት፡1,000 ተከታዮች (Subscribers) መስፈርት ሳይለወጥ እንዳለ ቀጥሏል።
ይህ እርምጃ ከፈረንጆች 2018 ወዲህ በዩቲዩብ የገቢ አስተዳደር ደንብ ላይ የተደረገ ትልቁ ማሻሻያ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ውስጥ የተካተቱ የአጭር ይዘት (Shorts) ፈጣሪዎች የገቢ ክፍያቸው እንዳይቋረጥ በየ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊየን እይታዎችን ጠብቀው መጓዝ እንዳለባቸው ተመላክቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1