ሳዑዲ በአንድ ሳምንት ውስጥ 940 ኢትዮጵያውያንን
በሕገወጥ ድንበር ጥሰት በቁጥጥር ሥር አዋለች
በሳዑዲ ዓረቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ይፋ በተደረገው መረጃ መሠረት፤ ሀገሪቱ በቅርቡ ባካሄደችው የድንበር ቁጥጥር ዘመቻ በሕገወጥ መንገድ ድንበር ለማቋረጥ የሞከሩ 940 ኢትዮጵያውያንን በአንድ ሳምንት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውላለች። ሚኒስቴሩ ከጁላይ 30 እስከ ኦገስት 5 ባለው ጊዜ ውስጥ ባካሄደው በዚህ ዘመቻ በጠቅላላው 1,593 ሕገወጥ ድንበር አቋራጮችን የያዘ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 59 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያውያን እና 40 በመቶ ያህሉ ደግሞ የየመን ዜጎች ናቸው። በዚሁ ሳምንት የመኖሪያና የሥራ ሕግ የጣሱ 14,440 ሰዎች የተያዙ ሲሆን፣ 10,827 ሕገወጥ ነዋሪዎች ደግሞ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ተደርገዋል።
የሳዑዲ ዓረቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አክሎ እንዳስታወቀው፤ ሕገወጥ ድንበር አቋራጮችን ሲያጓጉዙ፣ ሲሸሽጉ ወይም ሥራ ሲሰጡ የተገኙ 25 ግለሰቦችም ተይዘዋል። ሚኒስቴሩ በሰጠው ማስጠንቀቂያ፤ ሕገወጥ መግቢያን የሚያመቻቹ ወይም ጥሰተኞችን የሚያስጠጉ ሰዎች እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ የፅኑ እስራት፣ እስከ 1 ሚሊዮን የሳዑዲ ሪያል (260 ሺህ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ እንዲሁም የተጠቀሙባቸው ተሽከርካሪዎችና ንብረቶች መወረስ እንደሚጠብቃቸው አስታውቋል።
@Seledadotio

No comments yet.