‘E Pluribus Unum’
‘Out of many, One’
‘ One from many’
#Ethiopia | ….ውድ የሀገሬ ሰዎች! የገባንበት አዘቅት ግድግዳው ተንዶ ሳያዳፍነን ‘ቅንዑ ለእንተ ተዐቢ ፀጋ!’ አንዲል መጽሐፍ ከመንደርና ሰፈራችን ለምትልቀው ትልቋ ፀጋ ኢትየጵዊነት እንትጋ፡፡ ሀገር ካለን መንደርና ሰፈር ይኖረናል፣ ሀገር ስናጣ ግን ሁሉንም እናጣለን፡፡
አንዴ ለታደልነው እና ለማንለውጠው፣ ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ ፈጽሞ ለተሰጠን ማንነት አብዝተን ከመጨነቅ ይልቅ ለምንጨምረው፣ ለምናተርፈው፣ ትጋትን ለሚጠይቀው ኢትዮጵያዊ ማንነት እንበርታ፡፡ ፈጣሪ ኢትዮጵያን ሳይነሳን እኛ ኢትየጵያዊነትን ለራሳችን አንንፈግ፡፡
መንደራችንንና ሰፈራችንን ከተራራው ጥግ አስቀምጠን ወደ ተራራው ጫፍ ወደ ኢትየጵያዊነት እንውጣ፡፡ ከተራራው ጫፍ ስንደርስ ደግሞ ቀይ ባሕር ይታየናል፤ ፓን አፍሪካኒዝም፣ ዓለማቀፋዊነት ይጠብቀናል!!
በየማዕዘናቱ ነገ ልጆቻችን ሲረግጡት የሚፈነዳ ፈንጅ አንተው፤ ይልቁንም የልማትና የአንድነት አርማን እናስቀምጥላቸው፡፡ የግፍ ፅዋችን ሞልቶ ፈሷልና በበጎ መንፈስ ከእንግዲህ ለትብብር ፅዋችንን እናንሳ!…
‘E Plurius Unum!!!
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ
#unity #peace #ethiopianism #alemayehuwase #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.