#Ethiopia | በቡሬ ከተማ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ፍጹም አማረ የአካባቢው አርሶ አደሮች የሚያጋጥማቸውን የድካም፣ የጊዜ ብክነት እና የምርት ውድመት በቅርበት በመመልከት ለችግሩ ዘመናዊ መፍትሔ ማቅረብ ችሏል።
ታዳጊው ኢኮ ስፕሬይ ኤክስ የተሰኘች የግብርና ድሮን ቴክኖሎጂ የፈጠረ ሲሆን ይህች ድሮን በግብርናው ዘርፍ ውስጥ አራት ዋና ዋና ተግባራትን በአንድ ጊዜ የማከናወን ከፍተኛ ብቃት እንዳላት ገልጻለች።
የመጀመሪያው ተግባሯ ፀረተባይ ኬሚካል መርጨት ሲሆን ይህም አርሶ አደሮች ኬሚካሎችን በጀርባቸው ተሸክመው ያለ በቂ የጤና ጥንቃቄ በሚረጩበት ወቅት የሚደርስባቸውን የጤና ጉዳት እና የጊዜ ብክነት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።
ሁለተኛው ፈሳሽ ማዳበሪያን የማሰራጨት ስራ ሲሆን አርሶ አደሮች በባህላዊ መንገድ ማዳበሪያ ለመጨመር የሚያባክኑትን ጉልበት እና ጊዜ በመቀነስ በደቂቃዎች ውስጥ ሙሉ ማሳን ማዳረስ ያስችላል።
ሶስተኛው ተግባሯ ደግሞ ሰብል አጥፊ የሆኑ የአንበጣ መንጋዎችን እና ሌሎች ፀረሰብል ነፍሳትን በብቃት ማባረር ነው።
አራተኛው የመስኖ ውኃ እርጭት ሲሆን በባህላዊ የመስኖ ዘዴ ምክንያት የሚከሰትን የአፈር መሸርሸር እና የቡቃያዎችን ስር ለፀሐይ የመጋለጥ አደጋ በመከላከል ጥንቃቄ የተሞላበት ውኃ ማዳረስ ታከናውናለች።
ተማሪ ፍጹም ኬሚካል በቀን ውስጥ መረጨት እንደሌለበት በመጠቆም በቀን በሚረጭበት ወቅት ማር የሚሰበስቡ ንቦች ስለሚሞቱና የምርት መጠን ስለሚቀንስ ድሮኗ ከተፈጥሮ እና አካባቢ ጥበቃ ጋር በተጣጣመ መልኩ ማከናወን እንድትችል አድርጎ ቀርጿታል።
ይህንን ድሮን ለመስራት የተለያዩ ሞተሮች፣ ፓምፖች፣ ኖዝሎች እና የአልሙኒየም ማዕቀፎችን በፈጠራ ብቃቱ አስተካክሎ መጠቀሙን ከአሚኮ ጋር በነበረው ቆይታ አስረድቷል።
በወጣትነት እድሜ ላይ ሆኖ እንደዚህ ያለ አርቆ አስተዋይነት ያለው ሀገር በቀል መፍትሔ ማቅረቡ ለሀገሪቱ የቴክኖሎጂ እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ በመሆኑ እንደነዚህ ያሉ ባለሃሳቦችን መደገፍ እና ማበረታታት ይገባል።
AMECO
ሮዛ የሻነህ
#ethiopia #agriculture #technology #innovation #farmers #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.