የኤሎን መስክ የተጣራ ሀብት በስፔስኤክስ አክሲዮን ዕድገት ምክንያት ዳግም ከ800 ቢሊዮን ዶላር በላይ አለፈየስፔስኤክስ አክሲዮ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኤሎን መስክ የተጣራ ሀብት በስፔስኤክስ አክሲዮን ዕድገት ምክንያት ዳግም ከ800 ቢሊዮን ዶላር በላይ አለፈ
የስፔስኤክስ አክሲዮን በ15.8 በመቶ ማሻቀቡን ተከትሎ የኩባንያው የገበያ ዋጋ 1.75 ትሪሊዮን ዶላር ደርሷል። ይህንን ተከትሎም የኤሎን መስክ የተጣራ ሀብት በብሉምበርግ ቢሊየነሮች መረጃ ጠቋሚ 817 ቢሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም በፎርብስ መጽሔት 823.6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል።
የቅርብ ጊዜው የገበያ ንቅናቄ የመጣው ኩባንያው ካስመዘገበው ጠንካራ የሩብ ዓመት የገቢ አፈጻጸም በኋላ ሲሆን፣ የኩባንያው ገቢ ከታሰበው በላይ በመጨመር 7.8 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። የኦፕሬቲንግ ኪሳራውም ወደ 541 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ ማለት ችሏል።
በአርቴፊሻል ኢንተለጀንት (AI) መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ የ18.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ቢያደርግም፣ የባለሀብቶች እምነት ከፍተኛ ሆኖ ቀጥሏል። የስታርሊንክ ሳላይት ኢንተርኔት ገቢ በ66 በመቶ አድጎ 4.29 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ የክላውድ እና ኤአይ ክፍል ገቢ ደግሞ የ247 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቁሟል።
ስፔስኤክስ እጅግ ፈጣን ዕድገት በማሳየት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በታህሳስ ወር ዓመታዊ ገቢውን ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እና እስከ 2030 ድረስ ደግሞ 1 ትሪሊዮን ዶላር ገቢ ለማስመዝገብ ግብ ማስቀመጡ ተመላክቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: