ሦስት አሠልጣኞችና አራት አትሌቶች አሜሪካ ፖርትላንድ ላይ ኮበለሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

🔴

🔴ቡድኑ በቺካጎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲመለስ 7 የቡድኑ አባላት ከልዑካን ቡድኑ ጋር የሉም

🔴የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ቤቻ ሳትሆን በርካቶች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማም ሆና ተመዝግባለች

#Ethiopia | በአሜሪካ ኦሬገን ዩጂን ሲካሄድ የነበረው ከ20 ዓመት በታች 21ኛው የአለም አትሌቲክስ የወጣቶች ሻምፒዮና መጠናቀቁ ይታወሳል።

ወደ ውድድሩ ስፍራ የተጎዘችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣3 ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 6 ሜዳሊያ ማግኘቷም ይታወቃል።

ከወደ ኦሪገን ከደቂቃዎች በፊት የደረሠን አስደንጓጭ ዜና ለሻምፒዮናው ከተጓዙት የልዑኳን ቡድን አባላት መካከል ሰባቱ ሰባቱ ፖሬትላኔድ ላይ መኮብለላቸው ተረጋግጦል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን በአሁን ሠዓት ከፖርትላኔድ ተነስቶ ወደ ቺካጎ አየር ማረፊያ እየተጓዘ ሲሆን እነዚሁ ሰበመቱ የቡድኑ አባላት ከልዑኳን ቡድኑ ተለይተው መቅረታቸውን ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ያረጋገጠችው።

እንደ ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ከሄዱት አራት አሠልጣኞች ሶስቱ ከቡድኑ ጋር ባለመመለሳቸው ቀአሁን ሠዓት ወደ ኢትዮጵያ በመገስገስ ላይ በሚገኘው አውሮፕላን ውስጥ አንድ አሠልጣኝ ማለትም አሠልጣኝ መሠረት ብቻ እንደሚገኝ ነው ምንጮቻችን የገለፁልን።

አትሌትችን በተመለከተ አራት አትሌቶች እኔደኮበለሉ የገለፁሌን የመረጃ ምንጮቻችን በወኪንግ፣በ800፣በ5ሺ እና በ3ሺ መሠናክል ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ከቡድኑ ጋር አብረው እንዳልተመለሱና እንደኮበለሉ ነው የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው የገለፁልን።

የአትሌቶቹና የአሠልጣኞቹ ሙሉ ስም የደረሳት ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል ለቤተሠቦቻቸውና ለደህንነታቸው ስትል የሁሉንም ስም ይፋ ከማድረግ ተቆጥባለች።

የአሜሪካኗ ዩጂን ኦሪገን ለኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ውጤት የሚመዘገብባት ከተማ ቤቻ ሳትሆን በርካታ አትሌቶች፣አሠልጣኞችና አመራሮች የሚኮበልሉባት ታሪካዊ ከተማ ሆና ተመዝግባለች።

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: