የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ተሿሚ ፕሬዚዳንት ከተቋሙ አመራሮች ጋር የመጀመሪያ የሥራ ውይይት እና የትውውቅ መድረክ አዘጋጁ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቅርቡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ የተሾሙት ዶክተር የቻለ ከበደ ከጽሕፈት ቤታቸው ዳይሬክተሮችና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር የመጀመሪያ የትውውቅና የሥራ አቅጣጫ ማስጨበጫ ውይይት አድርገዋል።

በፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው በዚህ መድረክ፣ በከፍተኛ እና በመካከለኛ አመራሮች መካከል ግልጽና ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ በመፍጠር የተቀናጀ የአሠራር ሥርዓትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ውይይት ተካሂዷል።

ዶክተር የቻለ ከበደ በመድረኩ ባስተላለፉት መልእክት፣ የዩኒቨርሲቲውን ሀገራዊና ተቋማዊ ግቦች ለማሳካት የውስጥ አሠራርን ማጠናከር እንዲሁም በሕብረት የመሥራት ባህልን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

ተቋማዊ ውጤታማነት የሚረጋገጠው እያንዳንዱ አመራርና ሠራተኛ የተጣለበትን ኃላፊነት በከፍተኛ የባለቤትነት ስሜትና በጋራ ጥረት ሲወጣ መሆኑንም አሳስበዋል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን የአፈጻጸም አቅም ማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ በውጤት ተኮር አሠራር ላይ ትኩረት ማድረግ እና ሀብቶችን በቁጠባና በውጤታማነት ጥቅም ላይ ማዋል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

በውይይቱ የተሳተፉት አመራሮች በአዲሱ ፕሬዚዳንት የቀረቡትን የሥራ አቅጣጫዎች በመቀበል፣ የተጀመሩ ልማቶችን ለማስቀጠልና አዳዲስ አሠራሮችን በተግባር ለመተርጎም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በቀጣይም ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አካላት ጋር ተመሳሳይ የሥራ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ከተቋሙ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#GondarUniversity #Gondar #Education #HigherEducation
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: