በሆስፒታል ውስጥ ሰው ባለፈ ቁጥር አይኗ የሚንከራተተው የ4 ወር ሕፃን ልጅ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኤኳዶር ጓያኪል በሚገኘው ፍራንሲስኮ ደ ኢካዛ ቡስታማንቴ የሕፃናት ሆስፒታል ውስጥ የምትገኘው የአራት ወር ሕፃን አራት ወራትን በሆስፒታል ክፍል ውስጥ ለማሳለፍ ተገዳለች።

እስካሁን በሆስፒታል ውስጥ የምትገኘው ይህች ሕፃን አሁን በጥሩ ጤንነት ላይ የምትገኝ ቢሆንም በወላጆቿ እንደተ’ተወች በመጠረጠሩ ጉዳዩ በሕግ አካላት እየተጣራ ይገኛል።

​በአልጋዋ አጠገብ ሰው ባለፈ ቁጥር የሚታወቅ ፊት እንደመፈለግ ወይም የሚያነሳት ሰው እንደምትጠብቅ ሁሉ አንገቷን ቀና አድርጋ የምታይበት አጋጣሚ ልብ ይነካል።

ታሪኳ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ በኋላ በርካታ ሰዎች ሕፃኗን በጉዲፈቻ ለመውሰድ እና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎታቸውን የገለጹ ቢሆንም የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎች ግን የጉዲፈቻ ሂደቶችን የማያከናውኑ መሆኑንና በሕፃኗ ስም የተከፈተ የገንዘብ ማሰባሰቢያ አካውንት አለመኖሩን አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት የሕክምና ባለሙያዎች አስፈላጊውን እንክብካቤ እያደረጉላት የሚገኝ ሲሆን የሕፃኗን የወደፊት እጣ ፈንታ ለመወሰን እና አስተማማኝ መጠለያ ለማመቻቸት እየሠሩ ይገኛሉ።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: