“ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለውን ትርክት የፈጠረው ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ነው ሲሉ ጄነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja | ​በኬኒያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ ትናንት ምሽት ከአዲስ ኮምፓስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ ምልልስ፣ በግል ህይወታቸው እና በወታደራዊ አገልግሎታቸው ዙሪያ ለሚነሱ ትችቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

​አምባሳደሩ በዚሁ ቆይታቸው “ባጫ ዳንሰኛ ነው” የሚለውና በሰፊው የሚናፈሰው ትርክት ያለምንም ማስረጃ በሟቹ ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ የተቀናበረ መሆኑን ተናግረዋል። “ጄነራልነት የሰጠኝ ብሄራዊ ቲያትር አይደለም” ያሉት ጄነራል ባጫ፣ ምርኮኛም ሆነ ዳንሰኛ እንዳልሆኑ በመግለጽ “የማረከኝ አካል ካለም ይውጣና ይናገር” ሲሉ የቀረቡባቸውን ወቀሳዎች አስተባብለዋል።

​አክለውም ይህ አይነቱ ትችት በግል እሳቸው ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሳይሆን፣ ከወጡበት የብሄር ማንነት ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ስልታዊ ስም ማጥፋት እንደሆነ አብራርተዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2