ከ100 ሚሊዮን በላይ አረጋዊያን ያለ ጡረታ ቀርተዋል፦ የአለም የስራ ድርጅት

- Advertisement -
Sidebar AD

ከ850 ሚሊዮን አረጋውያን መካከል የጡረታ አበል የሚያገኙት 700 ሚሊዮኖቹ ናቸው ሲል ድርጅቱ ገልጿል።

#Ethiopia |እንደ ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት መረጃ መሠረት በዓለም ላይ ካሉ አረጋውያን መካከል መደበኛ የጡረታ ክፍያ የሚያገኙት 70 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ብሏል።

በመላው አለም በጡረታ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር ከ830 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል።

በአብዛኞቹ የዓለም ሀገራት መደበኛ የጡረታ ዕድሜ ከ60 እስከ 65 አመት እንደሆነ ተቀምጧል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ቁጥር 830 ሚሊዮን እስከ 850 ሚሊዮን ይጠጋል ይህም ከአለም አጠቃላይ ህዝብ 10 በመቶ ያህሉን ይይዛሉ።

ዕድሜያቸው ከ60 አመት በላይ የሆኑ ዜጎች ቁጥር 1.1 ቢሊዮን ይደርሳል።

ከዚህ ቁጥር ውስጥ የጡረታ ገቢ እያገኙ የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር 700 ሚሊየኖቹ ብቻ ናቸው።

ቀሪዎቹ በተለይ በታዳጊ ሀገራት ያሉ የጡረታ እድሜ ላይ ቢደርሱም የጡረታ አበል ስለሌላቸው በቤተሰብ ድጋፍ ወይም እስከ እርጅናቸው መጨረሻ ድረስ ሥራ በመሥራት ይኖራሉ ብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#ILO #retirement
#pension #economy
#Salary #professional


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: