#Ethiopia | የቀድሞ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የባንኩ ከፍተኛ ባለአክሲዮን መሆናቸው ተነገረ።
የቀድሞ የኬኒያ መንግስት ባለስልጣን የነበሩት ኤስቴር ጄፕኬምቦይ ኮይሜት 17 በመቶ ድርሻ በመያዝ የሜድል ኢስት ባንክ ኬንያ ከፍተኛ ባለአክሲዮን መሆናቸው ተገልጿል።
ኤስቴር ኮይሜት የያዙት የ17 በመቶ አክሲዮን ድርሻ በባንኩ ካሉ ዋና ዋና ኩባንያዎች በላይ እንደሚያደርጋቸው ይፋ የተደረጉ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ኮይሜት በኬንያ በፋይናንስ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የዳበረ ልምድ እንዳላቸውም ነው የሚነገረው።
አሁን ላይ በኬንያ ንግድ ባንኮች ውስጥ ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ካላቸው ጥቂት ሴት ባለሃብቶች መካከል አንዷም ሆነዋል።
ኤስቴር ኮይሜት ከአክሲዮን ባለቤትነታቸው ባሻገር ከየካቲት 2024 ጀምሮ በባንኩ የቦርድ አባልነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
በ2017 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አባታቸው ኒኮላስ ቢዎት የነበራቸውን ሀብት ለልጆቻቸው እኩል 14 ቦታ አካፍለው እንዲወርሱ አድርገው ነበር።
በፈረንጆቹ 2017 ላይ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት የባለስልጣኗ አባት ኒኮላስ ቢዎት የቀድሞ የኬኒያ የካቢኔ ሚኒስትር አባል ሆነው ሰርተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Kenya #Bank #finance
#government #investment
#Shareholders
Source: GetuTemesgen








No comments yet.