በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሀገራቸውን ሲወክሉ የቆዩት የኢትዮጵያ አትሌቶች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት በተካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

ኢትዮጵያ በዚሁ ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ 2 የወርቅ፣ 3 የብር እና 1 የነሐስ በድምሩ 6 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ከዓለም 5ኛ ደረጃን እንዲሁም ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች።

ይህ ታላቅ ሻምፒዮና በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ በሚገኘው ሄይዋርድ ፊልድ ስታዲየም ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።

#athletics #worldu20 #ethiopianathletics #sports
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1