“የኢትዮጵያ ወጣቶች የሉዓላዊነታችን ፅኑ ማገር ናቸው” አሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት …

- Advertisement -
Sidebar AD
“የኢትዮጵያ ወጣቶች የሉዓላዊነታችን ፅኑ ማገር ናቸው” አሉ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
 
ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት እንደማይቻል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፤ ወጣቱ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ድርሻ የሚይዝ እና የሁለንተናዊ እድገት መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት በሚከበረው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፦ “የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው” ብለዋል። አክለውም የአሁኑ ትውልድ የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
 
አሁን ያለው ወጣት ሀገርን ወደኋላ የሚያስቀሩ አጓጉል ልማዶችን፣ አላስፈላጊ ንትርኮችን እና ግጭቶችን በመራቅ ትኩረቱን በልማት ላይ ማድረጉንና ድህነትን የተጸየፈ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
 
በመጨረሻም ሀገራዊ ርዕይን ዕውን ለማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በንቃት እየተጋ በፍቅር እና በአንድነት እንዲመላለስ ጥሪ አቅርበዋል።
 
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1