#Ethiopia | ቦርዱ ባለፉት አራት አመታት በሀገሪቱ ባንኮች ኢንሹራንሶች እና ከ190 በላይ በሚሆኑ ድርጅቶች ላይ ያካሄደውን የኦዲት ጥራት ግምገማ ውጤት በይፋ ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ባለፉት 4 ዓመታት በሀገሪቱ ባንኮች ኢንሹራንሶች እና ከ190 በላይ በሚሆኑ የኦዲት ድርጅቶች ላይ ያካሄደውን አጠቃላይ የኦዲት ጥራት ግምገማ ውጤት በይፋ ይፋ አደረገ።
ቦርዱ እስካሁን ሲያደርግ የነበረውን የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጥ ምዕራፍ አጠናቆ ወደ ተጠያቂነት እርምጃ መሸጋገሩን አስታወቀ።
ቦርዱ ባካሄደው ጥልቅ ግምገማ በዘርፉ ላይ በርካታ አደገኛ ክፍተቶችን ማግኘቱን ነው ያስታወቀው።
አብዛኞቹ የኦዲት ስራዎች በቂ ማስረጃ ሳይኖራቸውና የተሰሩበት የሳምፕሊንግ ዘዴ በሰነድ ሳይደራጅ የሚከናወኑ መሆናቸውን ገልጿል።
የተሻሻሉ የኦዲት ስታንዳርዶችን አለመከተል የሙያ ሥነ-ምግባር እና የኦዲተሮች የነጻነት መርሆዎች መጣሳቸውም በውጤቱ ገልጿል።
የስራ ኃላፊዎችም ተገቢውን የቁጥጥር ስራ እንደማይሰሩም የግምገማ ውጤቱ ጠቁሟል።
የፋይናንስ ሪፖርቶች ጥራት ማነስ የኢንቨስተሮችን እምነት የሚሸረሽርና ሀገሪቷ በካፒታል ገበያ በምታደረገው ሽግግር ላይ ትልቅ ስጋት የሚፈጥር ነው ነው ሲል ቦርዱ አሳስቧል።
የግብር አሰባሰብ ውጤታማነት እና የካፒታል ገበያው መረጋጋት ቀጥታ ከኦዲት ጥራት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ቦርዱ ትኩረት እንዲሰጠው ሲል አስጠንቅቋል።
ከተሰጣቸው የማስተካከያ አስተያየት በኋላ እርምጃ ባልወሰዱ እና የኦዲት ጥራት ማሻሻያ ባላደረጉ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#AABE #የኦዲትጥራት #ኢትዮጵያ #ካፒታልገበያ #ባንክእናኢንሹራንስ #FinancialReporting #Accountability
Source: GetuTemesgen









No comments yet.