ደቡብ አፍሪካ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመመለስ ያወጣችውን ወጪ ኢትዮጵያ እንድትከፍል ጠየቀች‼️
ደቡብ አፍሪካ በተያዘው ዓመት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ካወጣችው ከ18 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የተወሰነውን ወጪ እንዲሸፍኑ ለኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ማላዊ ጥያቄ አቀረበች።
የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥያቄው መቅረቡን ይፋ ያደረገው ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፓርላማው የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ ወቅት ነው።
የቋሚ ኮሚቴው ዋና ዳይሬክተር ቶሚ ማኮዴ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴሩ ለዚህ ተግባር ቀደም ሲል የመደበው በጀት 60 ሚሊዮን ራንድ ብቻ ቢሆንም፣ እስካሁን 292 ሚሊዮን ራንድ ስደተኞችን ለመመለስ ወጪ አድርጓል።
ማኮዴ ስደተኞችን የመመለስ መርሃ-ግብር «በጀት ያልተያዘለት ኃላፊነት» መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለዚህ ያህል ሰፊ እንቅስቃሴ በጀት እንዳልመደቡ ተናግረዋል።
አክለውም የትራንስፖርት ክፍያው ወጪው ከፍተኛ እንዲሆን ዋና ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.