ሴት የመስተንግዶ ሰራተኞችን አለባበስ እና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ በአዲስ አበባ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረጉ ተነገረበከ5 ሺህ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ሴት የመስተንግዶ ሰራተኞችን አለባበስ እና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ በአዲስ አበባ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መደረጉ ተነገረ
በከ5 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮን ጨምሮ ሌሎች ቅጣቶችን የሚያስከትለው ሴት መስተንግዶ ሰራተኞች አለባበስ እና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሆነ የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር ለአሐዱ ሬድዮ አስታውቋል።
በ2017 ዓ.ም. ህዳር ወር ላይ በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ የወጣው ደንብ ቁጥር 178/2017፤ የደረት ክፍልን ያልሸፈነ ሸሚዝ፣ ከጉልበት በላይ የሆነ ጉርድ ቀሚስ እና ከጋብቻ ቀለበት ውጪ በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ጌጣጌጥ ማድረግን ይከለክላል።
የማኅበሩ መስራች እና ስራ አስፈጻሚ አባል ናፍቆት ጌታሁን፤ “በአንዳንድ ተቋማት የመስተንግዶ ሰራተኞች እንዲለብሱ የሚገደዱት መለያ ልብስ (ዩኒፎርም) ከባህል ያፈነገጡ ነበሩ” ብለዋል።
ይህንን ለማስተካከልም ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን ደንቡ እንዲጸድቅ ግፊት አድርጓል።
አሁን ላይ ደንቡ ጸድቆ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ ተግባራዊ ያልተደረባቸው ቦታዎች ካሉ ከመንግስት ክትትል በተጨማሪ ማኅበሩም አፈጻጸሙን እንደሚከታተል ተናግረዋል።
መመሪያው ያልተገበሩ የማኅበሩ አባላት ሲገኙ ለአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ሪፖርት እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን የቀረበ ሪፖርት እንደሌለ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በባር፣ በሬስቶራንት እና በሆቴሎች የሚለበሱ መለያ ልብሶች ጨዋነትን በጠበቀ መልኩ እንዲዘጋጁ እየተደረገ ነው ተብሏል።አሐዱ ሬዲዮ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1