በአዲስ አበባ ከተማ የ26 ዓመቷ እናት አራት ህፃናትን በአንድ ጊዜ በሰላም ተገላገለች።
በአዲስ አበባ በሚገኘው ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የ26 ዓመቷ እናት አራት ህፃናትን በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏ ተሰምቷል።
እናትየዋ አራት ፅንሶችን መፀነሷ በእርግዝና ክትትል ወቅት መለየቱን የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር እሸቱ ታደለ ገልጸዋል።
አራት ፅንሶችን የያዘ እርግዝና ለእናቲቱም ሆነ ለሚወለዱት ህፃናት ከፍተኛ ክትትልና ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ የወሊድ ቀኗ ከመድረሱ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ በሆስፒታሉ ዋርድ እንድትቆይ ተደርጎ የሌት ተቀን ክትትል ሲደረግላት ቆይታለች።
በወሊድ ወቅትም ለአራቱ ጨቅላ ህፃናት የሚያስፈልጉ ማረፊያዎችና የድጋፍ መሳሪያዎች አስቀድመው መዘጋጀታቸውን ዶ/ር እሸቱ መግለፃቸውን ብስራት ሬዲዮ ከጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
በዶ/ር እሸቱ ታደለና በማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ናትናኤል የተመራው የህክምና ቡድን የቀዶ ጥገና ሂደቱን በስኬት ማጠናቀቁን ሆስፒታሉ አስታውቋል።እናትየው እና አራቱ ህፃናት በአሁኑ ወቅት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በሆስፒታሉ ከሦስት ዓመት በፊት የ24 ዓመቷ እናት በሪፈር ከጤና ጣቢያ መጥታ አራት ህፃናትን በሰላም መገላገሏ ተገልጿል።
ተቋሙ በዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂና መሳሪያዎች የተደራጀ ሲሆን በየህክምናው ዘርፍ የተሰማሩ ስፔሻሊስቶችና ቁርጠኛ የጤና ባለሙያዎች መኖራቸው ለተሳካው የህክምና ሂደት አስተዋፅዖ አድርጓል ተብሏል።
ሆስፒታሉ በተለይም ለእናቶችና ህፃናት ጤና ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ እና እንደዚህ ያሉ ከፍተኛ ጥንቃቄና ልዩ ክትትል የሚፈልጉ እርግዝናዎችን በተሳካ ሁኔታ ማስተናገድ የ“እናት ጤና፣ ልጅም ደህና” የሚለውን የጤና መርህ በተግባር ማዋል አንዱ ማሳያ ነው ተብሏል።
@Seledadotio

No comments yet.