የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ፕሬዚዳንት ከአመራሮች ጋር የመጀመሪያ የትውውቅና የሥራ አቅጣጫ ውይይት አካሄዱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በቅርቡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት ዶ/ር የቻለ ከበደ ከጽሕፈት ቤታቸው ዳይሬክተሮችና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር የመጀመሪያ የትውውቅና የሥራ አቅጣጫ ማሰጫ መርሃ ግብር አካሄዱ።

በፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ መድረክ፣ በዋናነት በከፍተኛው አመራርና በመካከለኛ አመራሮች መካከል ግልጽና ውጤታማ የግንኙነት መስመር በመዘርጋት ቅንጅታዊ የአሠራር ባህልን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመግቢያ ውይይት ተደርጓል።

ዶክተር የቻለ ከበደ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር የዩኒቨርሲቲውን ሀገራዊና ተቋማዊ ተልዕኮ ለማሳካት የውስጥ አሠራርን ማጠናከርና በቡድን የመሥራት ባህልን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋማዊ ስኬት የሚረጋገጠው እያንዳንዱ አመራርና ባለሙያ የተጣለበትን ኃላፊነት በከፍተኛ የባለቤትነት ስሜት፣ በቅንጅትና በጋራ ጥረት ሲወጣ መሆኑንም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በውይይቱ ወቅት የተቋሙን የአፈጻጸም ብቃት ማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ በውጤት ተኮር አሠራር ላይ ትኩረት ማድረግ እና ያሉትን ሀብቶች በቁጠባና በውጤታማነት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችሉ ሀሳቦች ቀርበው ምክክር ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት አመራሮች በአዲሱ ፕሬዚዳንት የቀረበውን አቅጣጫ በመቀበል የተጀመሩ ሥራዎችን ለማስቀጠልና አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር በሙሉ ትጋት ለመሥራት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንቱ በቀጣይም ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ የሥራ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ከተቋሙ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።



Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1