አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ወንድ ልጅ መገላገሏን አበሰረች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በዓለም አቀፍ ደረጃ በሩጫ ስፖርት በርካታ ድሎችን ያስመዘገበችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ የመጀመሪያ ወንድ ልጇን በሰላም መገላገሏን ዛሬ ይፋ አድርጋለች።

​አትሌቷ በደስታ የተሞላውን የሕይወት ምዕራፍ በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ፣ የልጇን መወለድ በሰላምና በጤና ያበሰረች ሲሆን በእርግዝናዋ ወቅትና በፅናት በታገለችባቸው አታካች የሕይወት መንገዶች ውስጥ ያልተለያት የደጋፊዎቿና የመላው ኢትዮጵያውያን ጸሎትና ድጋፍ ትልቅ ብርሃን እንደሆናት ገልጻለች።

ፈጣሪ የእናትነትን አክሊል ስላጎናፀፋት ምስጋናዋን ያቀረበችው አትሌት ጉዳፍ፣ ውድ ደጋፊዎቿ አዲሱን ልጇን በጸሎታቸው እንዲያስቡላትና በቤታቸውም ሰላምና በረከት እንዲበዛ ተመኝታለች።

“ዛሬ በአርሴማ ቀን የዓለማት ጌታ በታላቅ ምህረቱና ቸርነቱ ወንድ ልጃችንን በሰላም አቅፌ እንድስም አድርጎኛል።”


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: