#Ethiopia | የቀድሞው የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዙ ሮንግጂ በ98 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
የቀድሞው የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ዙ ሮንግጂ በ98 ዓመታቸው በሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል።
ዙ ሮንግጂ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ የ14ኛው እና የ15ኛው ማዕከላዊ ኮሚቴ የፖሊት ቢሮ ቋሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ያገለገሉ ከፍተኛ የመንግሥት መሪ ነበሩ።
የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ የብሔራዊ ሕዝባዊ ኮንግረስ ቋሚ ኮሚቴ፣ የሕዝብ ግዛት ምክር ቤት እና የቻይና ሕዝቦች ፖለቲካዊ አማካሪ ጉባኤ ይፋዊ የሐዘን መግለጫቸው አውጥተዋል።
ምስጉን የፓርቲ መሪ፣ በፈተና ነጥረው የወጡ ታማኝ የኮሙኒስት ታጋይ፣ እንዲሁም የፓርቲው እና የሀገሪቱ የላቀ አብዮተኛ መሪ ነበሩ ሲል ሲጂቲኤን አስነብቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#China #ZhuRongji
#premier #died
#CPC #minister
Source: GetuTemesgen







No comments yet.