ሀላንድ በጊነስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ውስጥ ተካተተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​አዲሱ የእግር ኳስ ውድድር ዘመን ከመጀመሩ አስቀድሞ በርካታ የምንግዜም ድንቅ የጎል ማስቆጠር ሪኮርዶችን የጨበጠው ኖርዌያዊው የፊት መስመር አጥቂ አርሊንግ ብራውት ሀላንድ እስካሁን በእግር ኳስ ሕይወቱ ላስመዘገባቸው አስደናቂ ስኬቶች የጊነስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ የክብር ምስክር ወረቀቶች ተበርክተውለታል።

​ሀላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ111 ጨዋታዎች ብቻ 100 ጎሎችን በማስቆጠር ፈጣኑ ተጫዋች ከመሆኑም በላይ በአንድ የውድድር ዘመን 36 ጎሎችን በማስቆጠር የሊጉን የምንግዜም ከፍተኛ የጎል ሪኮርድ ማስመዝገብ ችሏል።

በተጨማሪም በዩኢኤፍ ኤ ሊግ 19 ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነ ሲሆን በአንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ 5 ጎሎችን በማስቆጠር ከሊዮኔል ሜሲ እና ሉዊዝ አድሪያኖ ጋር የሚጋራውን ድንቅ ሪኮርድ ጨምሮ ስሙን በጊነስ መዝገብ ላይ በደማቁ ሊያሰፍር ችሏል።

እነዚህ የኮከቡ ድንቅ ስኬቶች መጪው ጥቅምት 8 ቀን ይፋ በሚደረገው የጊነስ የዓለም ድንቅ መዝገብ የእግር ኳስ ዕትም ላይ ተካተው ለንባብ እንደሚበቁ ተገልጿል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: