ባራክ ኦባማ አዲስ የፖድካስት ፖሮግራም ይዘው ብቅ አሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia |ባራክ ኦባማ በሕይወታቸው ላይ ተፅዕኖ ስላሳደሩ መጻሕፍት የሚያወሳ አዲስ ፖድካስት ይፋ አደረጉ።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአስተሳሰባቸው በሕይወት ጉዟቸው እና በፖለቲካ አቋማቸው ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ያሳደሩ መጻሕፍትን የሚያስተዋውቁበትና የሚያወያዩበት አዲስ የፖድካስት ፕሮግራም ይፋ ማድረጋቸው ተገለፀ።

ኦባማ በመጻሕፍት ወዳጅነታቸውና በዓመታዊ የመጻሕፍት ጥቆማዎቻቸው ይታወቃሉ።

ባራክ ኦባማ በዚህ አየር ላይ በዋለው ፕሮግራማቸው አማካይነት በህይወታቸው ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸውን ደራሲያን ያቀርባሉም ተብሏል።

የደራሲያኑ ሥራዎቻቸው እና መጽሐፍቶቻቸው ያሳደሩባቸውን ተጽዕኖ ከሙያ አጋሮቻቸው እና ከአድማጮች ጋር ይጋራሉ ተብሏል።

የዚህ ፖድካስት ፕሮግራም አላማ በኦባማ አስተሳሰብና ስብዕና ግንባታ ላይ አሻራ ያረፉ መጻሕፍት እና ደራሲያንን መዳሰስ።

እንደዚሁም ለመጻሕፍት አፍቃሪያን ለአንባቢዎችና ለአዲሱ ትውልድ የንባብ ባህል ለመፍጠር ያለመ ነው ሲል ዘ ኢንዲፔንደንት አስነብቧል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#USA #BarackObama
#Media #podcast #program
#President #Book


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: