የ2026 የፀሐይ ግርዶሽ በአውሮፓን

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአውሮፓ የተለያዩ ክፍሎች አህጉሪቱን በከፊል እና በሙሉ ጨለማ ውስጥ የሚክተው የ2026 የፀሐይ ግርዶሽ ክስተት በመከናወን ላይ ይገኛል።

ጨረቃ በምድር እና በፀሐይ መካከል በመግባት የፀሐይን ብርሃን በሙሉ እና በከፊል የምትጋርድበት ይህ አጋጣሚ ከሰሜን ሩሲያ፣ ግሪንላንድ፣ አይስላንድ እንዲሁም ከስፔን እና ፖርቱጋል በግልጽ እንደሚታይ ተገልጿል።

በተለይም በለንደን የሚገኘው የሮያል ግሪንዊች ኦብዘርቫቶሪ ክስተቱን በቴሌስኮፕ በማስደገፍ የቀጥታ ስርጭት በማቅረብ ላይ ይገኛል።

በሂደቱም ጨረቃ የፀሐይን 90 በመቶ ያህል አካል በመሸፈን ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደምትደርስ ተመልክቷል።

ይህ የፀሐይ ግርዶሽ በምዕራብ እና በማዕከላዊ አውሮፓ ከፈረንሳይ አቆጣጠር 1999 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሙሉ ደረጃ የሚታይ ብርቅዬ ተፈጥሯዊ ክስተት እንደሆነ የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ገልፀዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#solareclipse #solareclipse2026 #astronomy #science #nature #europe #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: