#Ethiopia | ቺፕሶች እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሀገራት ደህንነት እና የፖለቲካ የበላይነት የሚወስን ዋነኛ አጀንዳ መሆኑ ተነገረ።
አቶሚክ ቦምብ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የዓለምን የኃይል ሚዛን እንደቀየረው ሁሉ በዚህ ዘመን ደግሞ ከሩዝ ቅንጣት ያነሱት ቺፕሶች እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት አዲስ የውጊያ ሜዳ ሆነዋል።
የዚህ ታላቅ እና እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ዋነኛ ተዋናዮቹ ደግሞ ሁለቱ የዓለማችን ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤቶች አሜሪካና ቻይና ናቸው።
ቀደም ሲል ለኮምፒውተር ለሞባይል እና ለቤት ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ብቻ ይውሉ የነበሩት እነዚህ ጥቃቅን ቺፖች ዛሬ ላይ የሀገራት ዕጣ ፋንታ ወሳኝ ናቸው።
የሀገራትን መከላከያ፣ የሳይበር ደህንነት እና የወደፊት የብሔራዊ ህልውና ዕጣ ፋንታ የሚወስኑ መገዳደያ እና መከላከያ መሳሪያዎች ሆነው ብቅ ብለዋል።
ዘመናዊ ድሮኖች፣ የረጅም ርቀት ሚሳይሎች፣ የስለላ አውታሮች እና የጠፈር ቴክኖሎጂዎች የሚንቀሳቀሱት በዚሁ ጥቃቅን ቺፕሶች አቅም ነው።
ቴክኖሎጂውን አስቀድሞ የተቆጣጠረ ሀገር የነገውን ዓለም በወታደራዊ ሀይል የመምራት አቅሙ ከፍተኛ ያደርገዋል።
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፍጥነት እና ጥራት ሙሉ በሙሉ የሚወሰነው በሚጠቀመው የቺፕስ ብቃት ላይ ነው።
ይህ ደግሞ ሁለቱን ሀገራት የሞት ሽረት ፍልሚያ ውስጥ እንዲገቡ አስገድዷቸዋል።
ውጥረቱ ወደ ከፋ ደረጃ የተሸጋገረው ሁለቱ ሀገራት በሚከተሏቸውን ጥብቅ ስልታዊ እርምጃዎች ምክንያት ነው።
ዋሽንግተን የላቁ የAI ቺፖች እና የቺፕ ማምረቻ ማሽኖች ወደ ቻይና እንዳይላኩ ጥብቅ ኤክስፖርት እገዳ ጥላለች።
ዓላማዋም የቻይናን የወታደራዊ እና የቴክኖሎጂ እድገት ገና ከስሩ ማገደ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚናገሩት።
ቤጂንግ በበኩሏ የአሜሪካ እገዳ ከእቁብ አልቆጠረችውም እንዲያውም ድምጿን አጥፍታ ነገዋን እየሰራች ትገኛለች።
ሀገሪቷ በመቶ ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር በጀት መድባ የራሷን የላቁ ቺፖች ለማምረት ሌት ተቀን እየሰራች ትገኛለች።
በተጨማሪም ለከፍተኛ ቴክኖሎጂ አስፈላጊ የሆኑትን ወሳኝ ማዕድናት ወደ ምዕራባውያን እንዳይላኩ በመከልከል የመልስ ምት እየሰጠች ትገኛለች።
የዚህ ሁሉ ውጥረት ማዕከል እና የጂኦ ፖለቲካው ስጋት እምብርት የሆነችው ደግሞ ታይዋን ናት።
ምክንያቱም የዓለም ከ90 በመቶ በላይ የላቁ ሴሚኮንዳክተሮች የምታመርተው እሷ በመሆኗ ነው።
ይህ አሜሪካ እና ቻይና የገቡበት ፍልሚያ ተራ የኢኮኖሚ ውዝግብ አይደለም።
ይልቁንም የ21ኛውን ክፍለ ዘመን የዓለም ፖለቲካ የሚመራው ማነው?
የነገውን የዓለም የደህንነት እና የወታደራዊ ሚዛን የሚቆጣጠረውስ ማን ነው?
ለሚሉትን ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ እና የዓለምን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን አዲሱ የቴክኖሎጂ ጦርነት በመሆኑ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Usa #China #AI #CHIPS #politics #economy #strategy #policy #sanction
Source: GetuTemesgen









No comments yet.