የላም ሽንት በሊትር 20 ሩፒ፦ በህንድ አርሶ አደሮች በላም ሽንት ሽያጭ ገቢ ማግኘት ጀመሩ!በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት የሚገኙ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የላም ሽንት በሊትር 20 ሩፒ፦ በህንድ አርሶ አደሮች በላም ሽንት ሽያጭ ገቢ ማግኘት ጀመሩ!
በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት የሚገኙ አርሶ አደሮች ከወተት በተጨማሪ ከላም ሽንት ሽያጭ ተጨማሪ ገቢ የሚያገኙበት አዲስ የሙከራ ፕሮጀክት ተጀምሯል።
በቡላንድሻህር ወረዳ በሚገኙ 15 መንደሮች ውስጥ የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት፡ አርሶ አደሮች የሚያስረክቡትን የላም ሽንት በሊትር እስከ 20 ሩፒ ለመግዛት አቅዶ እንቅስቃሴ ጀምሯል።
በአሁኑ ወቅት በየቀኑ አምስት መቶ ሊትር ያህል የላም ሽንት ከየአካባቢው እየተሰበሰበ ይገኛል። ለዚህም ሲባል በመንደሮቹ ውስጥ እስከ ሁለት መቶ ሊትር የመያዝ አቅም ያላቸው ልዩ ማከማቻ ታንከሮች ተተክለዋል።
ይህ የተሰበሰበው የላም ሽንት ለተፈጥሮ ማዳበሪያና ለተፈጥሮአዊ የፀረ-ተባይ መድሃኒቶች ዝግጅት የሚውል ሲሆን፡ ፕሮጀክቱ የአፈርን ለምነት ከመጠበቁ ባሻገር የአካባቢውን አርሶ አደሮች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ያሳድጋል ተብሎ ተጠብቋል።
የሙከራ ፕሮጀክቱ ውጤታማነት እየታየ ወደ ሌሎች ግዛቶች እንደሚሰፋ ተገልጿል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: