#Ethiopia | ዝነኛዋ የሆሊውድ አቀንቃኝ ቴለር ስዊፍት ስህተት ወይም ጎጂ ነው ብለን ያሰብነውን ሃሳብ በጽናት መሞገት እንችላለን ነገር ግን ያንን ሃሳብ ያቀረበውን ሰው እንደ ዋና ጠላት አድርጎ መፈረጅ አስፈላጊ አይደለም ብላለች።
በዕለት ተዕለት ሕይወታችን በሶሻል ሚዲያም ሆነ በማኅበራዊ ግኑኝነቶቻችን ውስጥ ከሰዎች ጋር አለመስማማታችን የማይቀር እውነታ ነው።
ነገር ግን ትልቁ ፈተና የሃሳብ ልዩነቱ ሳይሆን በምንለያይበት ወቅት ለሰዎች የምንሰጠው ምላሽ እና የምናሳየው አክብሮት ነው ስትል ተናግራለች።
የምናምንበትን እውነት ለማስጠበቅ በሚደረግ ክርክር ውስጥ ከፊት ለፊታችን ያለው ሰው ጥፋተኛ ሳይሆን የራሱ አመለካከት ያለው የሰው ልጅ መሆኑን መዘንጋት እንደሌለብን ነው የተናገረችው።
ከማንም ጋር በሁሉም ነገር የመስማማት ግዴታ የለብንም ነገር ግን ልዩነታችንን የምንገልጽበት መንገድ የራሳችንን ስብዕና እና ስልጣኔ ያሳያልም ብላለች።
ቴለር ስዊፍት እንዲህ ትላለች “ሰብዓዊነትን ሳናጓድል ሃሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እንችላለን” የሚል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Usa #taylorswift
#difference #singer
#idea #Debate #Humanity
Source: GetuTemesgen









No comments yet.