#Ethiopia | ሶማሊያው ዳኛ ኡመር አርታን ትላንት ከተደረገው የዩኤፋ ሱፐር ካፕ ጨዋታ በኋላ ዩኤፋን አመስግናለሁ ብለዋል።
በአሜሪካ የጉዞ ገደብ ምክንያት በዓለም ዋንጫ ላይ የመዳኘት ህልማቸው የተሰናከለባቸው ሶማሊያው ዳኛ ኡመር አርታን የዩኤፋ ሱፐር ካፕ ጨዋታ ትልቅና የማይረሳ ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖላቸዋል።
ዳኛ ኡመር አርታን ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ ይህ ለእኔ የአለም ዋንጫዬ ነበር ዩኤፋ ህይወቴን የተሻለ ስላደረገልኝ አመሰግናለሁ ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በአሜሪካ የቪዛ እና የጉዞ ገደብ ምክንያት በዓለም ዋንጫው ላይ የመሳተፍ እድል አጥተው የነበሩት አርታን ዩኤፋ የሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ የመዳኘት አጋጣሚ ማግኘታቸው ህልማቸውን እንዲያሳኩ አድርጓቸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#UEFA #Worldcup
#Somali #referee #OmarArtan
Source: GetuTemesgen









No comments yet.