“ጥቃት አድርሰህብኝ ስታበቃ ፤ ራሴን በተከላከልኩ ካሳ ክፈይ ብሎ ነገር ምንድን ነው?” — ጆርጂያ ሜሎኒ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ “ጥቃት አድርሰህብኝ ራሴን ከተከላከልኩ በኋላ ለምን ክፍያ እከፍልሃለሁ?” በማለት በሀገሪቱ ከፍተኛ ክርክር ያስነሳውን አዲስ የሕግ ማሻሻያ ተከላክለዋል።

በጣሊያን አዲስ በተደነገገው ሕግ መሠረት ወንጀል በመፈጸም ላይ ሳለ ራሱን በተከላካዩ ተጎጂ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ማንኛውም ወንጀለኛ ወይም ቤተሰቦቹ ከተጎጂው የካሳ ክፍያ መጠየቅ አይችሉም።

​ይህ ማሻሻያ የተደረገው የመኖሪያ ቤት ስርቆት ወይም ጥቃት የደረሰባቸው ተጎጂዎች ራሳቸውን በመከላከል ሂደት በአጥቂዎቻቸው ላይ ላደረሱት ጉዳት በፍርድ ቤት የካሳ ክስ ሲመሰረትባቸው የቆዩባቸውንና የሕዝብ ቁጣ ያስነሱ ክስተቶችን ለመግታት ነው።

የጣሊያን መንግሥት ይህንን ሁኔታ አጣዳፊ ማስተካከያ የሚያስፈልገው “ያልተገባ አሰራር” ሲል የገለጸው ሲሆን ሕጉ የወንጀለኞችን መብት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ሳይሆን ራሱን በተከላካይ ተጎጂ ላይ የሚቀርብን የካሳ ጥያቄ ብቻ የሚከለክል እንደሆነ ተብራርቷል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: