በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ዋና ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሚተላለፈው ታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል።
ከተመዘገቡት ጥሰቶች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀይ መብራት ጥሶ ማለፍ ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ከ900 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚንቀሳቀሱም ተመልክቷል።
ዋና ኢንስፔክተሩ የትራፊክ ሕግን አለማክበር ለሕይወትና ንብረት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አሳስበው፤ የቁጥጥርና የቅጣት አፈጻጸሙ መጠናከሩ ግን አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ውጤት እያሳየ ይገኛል ብለዋል።
በዚሁ መሠረት በ2017 ዓ.ም 4መቶ11 የነበረው የሞት አደጋ በ2018 ዓ.ም ወደ 3መቶ82፤ የከባድ አደጋዎች ቁጥር ደግሞ ከ1 ሺህ9መቶ85 ወደ 1ሺህ8መቶ65 ዝቅ በማለት የ1መቶ20 አደጋዎች ቅናሽ አሳይቷል።
በአንጻሩ ቀላል አደጋዎች ከ1መቶ15 ወደ 7መቶ35፣ የንብረት ጉዳቶች ደግሞ ከ34 ሺህ84 ወደ 34 ሺህ7መቶ2 ከፍ ብለዋል።
በመጨረሻም አሽከርካሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ሕግን በማክበር ማሽከርከር እንዳለባቸው እና የሰው ሕይወትና ንብረትን ከውድመት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሳራ ዮሐንስ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.