#Ethiopia | በኦስትሪያ ቪየና ከተማ በድንገት የተሰወሩትን ሁለቱን እስራኤላውያን ሴቶች ለማግኘት በሚደረገው ጥረት የሀገሪቱ የደህንነት ተቋም ሞሳድ እገዛ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
የእስራኤል ባለስልጣናት እና የቪየና ፖሊስ እንዳስታወቁት፣ የሴቶቹ መጥፋት ከአሸባሪነት፣ ከብሔረተኝነት ወይም ከወንጀል ድርጊት ጋር የተያያዘ ለመሆኑ እስካሁን ምንም አይነት ጥርጣሬና ማስረጃ አልተገኘም።
ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሆኑት እናት ማሊ ያሃሎሚ እና የ23 ዓመት ልጃቸው ሊኤል ያሃሎሚ በፕራግ የጀመሩትን የልደት ቀን ጉዞ በባቡር ወደ ቪየና ካደረጉ በኋላ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም (ኦገስት 7 ቀን 2026) ደብዛቸው መጥፋቱ ይታወቃል።
የእስራኤል የደህንነት አካላት ባካሄዱት የመጀመሪያ ደረጃ ማጣሪያ፣ በክስተቱ ላይ የፕሮ-ፓለስታይን ወይም የኢራን ቡድኖች እጅ እንዳለበት የሚያሳይ ምንም አይነት ፍንጭ አለመኖሩ ተረጋግጧል።
የኦስትሪያ ፖሊስ በበኩሉ የወንጀል ድርጊት ጥርጣሬ የለም ቢልም፣ ምርመራውን ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማሸጋገር ሊኖሩ የሚችሉ ሁሉንም አጋጣሚዎች በመፈተሽ ላይ ይገኛል።
አሁን ላይ የፍለጋ እንቅስቃሴው የሴቶቹን ስልክ አድራሻ በመከታተል እና በአካባቢው በሚገኙ ሆስፒታሎች ላይ በማተኮር እየተከናወነ ነው።
የፍለጋ ሂደቱን በዋናነት እየመራ የሚገኘው የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን፣ ይህም ክስተቱ ከደህንነት ስጋት ይልቅ ሲቪላዊ አጋጣሚ ለመሆኑ ማረጋገጫ ተደርጎ ተወስዷል። ሆኖም የደህንነት ተቋሙ ሞሳድ በፍለጋው ጥረት ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።
የእስራኤል ፖሊስ ኮሚሽነር ዳኒ ሌቪ በጉዳዩ ላይ የላቀ የስራ ግምገማ ካካሄዱ በኋላ፣ በእስራኤልም ሆነ በውጭ ሀገራት ያሉ የፖሊስ አቅሞችና ዘዴዎች በሙሉ ጥቅም ላይ እንዲውሉ መመሪያ አስተላልፈዋል።
የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤን ጊቪር በበኩላቸው ከተጠፋፊዎቹ ቤተሰቦች ጋር ተነጋግረው አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግ እና ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተሉት አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#እስራኤል #ኦስትሪያ #ቪየና #ሞሳድ #ዜና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.