#Ethiopia | ከገቢ አሰባሰብ ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀልና በኢኮኖሚ አሻጥር የተጠረጠሩ 41 የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ተባባሪዎቻቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ፖሊስ የተፈጸመው ድርጊት በቡድን የተደራጀና ውስብስብ በመሆኑ፣ የጠፋውን የገንዘብ መጠን በኦዲት ለማረጋገጥ እንዲሁም የተሟላ ማጣሪያ በማካሄድ የምርመራ መዝገቡን ለማዘጋጀት የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
በወንጀሉ የደረሰውን የጉዳት መጠን በሂደት ይፋ እንደሚያደርግ የጠቆመው ፖሊስ፣ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢለቀቁ የምስክሮች ቃል እንዲቀየር ሊያደርጉና ማስረጃዎችን ሊያጠፉ ይችላሉ በሚል የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል።
የተጠርጣሪዎች ሕጋዊ ተወካዮች ደንበኞቻቸው በዋስ የመፈታት መብታቸው እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም፣ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ስጋትና ጥርጣሬ አሳማኝነት በመቀበል የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
በዚህም መሠረት ፖሊስ የምርመራ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ከሐምሌ 30 እና ነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ የሚሰላ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።
ከዚህ በተጨማሪም ችሎቱ የተጠርጣሪዎች አያያዝና የጤና ሁኔታ በትክክል እንዲጠበቅ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን፣ የምርመራውን ሂደት ለማየትም ለነሐሴ 14 እና 15 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
#የሙስናወንጀል #የገቢዎችሚኒስቴር #ፍርድቤት #ዜና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.