#Ethiopia | የግዙፉ የዋልማርት ኩባንያ ወራሽ የሆነችው አሊስ ዋልተን አጠቃላይ የሃብት መጠኗን ወደ 122 ቢሊዮን ዶላር በማሳደግ ከእንስቶች ቀዳሚ ሆናለች።
አሊስ ዋልተን ስኬት ማለት የተሰጠህን እድል መጠቀም ብቻ ሳይሆን ያንን እድል ተስፋ ለቆረጡና ለሌሎች መትረፊያ ማድረግ መቻል ነው ትላለች።
አሊስ አሁን ላይ የዓለማችን ቁጥር አንድ እንስት ባለሃብት መሆን ችላለች።
አሊስ ዋልተን ከፈረንሳይዋ ፍራንሷ ቤታንኩር በልጣ የዓለማችን ቁጥር አንድ እንስት ባለሃብት ዝርዝር አናት ላይ መቀመጥ የቻለችው።
አሊስ ከንግድ ዓለሙ በተጨማሪ በኪነ ጥበብ እና በግዙፍ በጎ አድራጎት ስራዎቿ ትታወቃለች።
የቤተሰቧን ንግድ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ረገድ የነበራት የዘርፈ ብዙ ኢንቨስትመንት እይታ ለዚህ ስኬቷ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል ነው የተባለው።
አሊስ ዋልተን የዋልማርት መስራች የሳም ዋልተን ልጅ ስትሆን ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ በንግዱ ዘርፍ ላይ ከማድረግ አልፋ የራሷን አለም ወደ መፍጠር ተሸጋግራለች።
አሊስ የጥበብ ሙዚየሞችን በመገንባትና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በመደገፍ የራሷን አሻራ እያሳረፈች ትገኛለች።
አሊስ በፎርብስ የአለም የሀብታሞች ስም ዝርዝር ውስጥ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Forbes #wealthiest
#women #Walmart
#AlisWalton #investment
Source: GetuTemesgen








No comments yet.