ዜናውን በአግባቡ ካልሰራችሁ የታሪኩ አካል አትሆኑም!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሀገራዊ ምክክር መጀመር ትልቅ ዜና ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊያን በተለያየ አጀንዳዎች ልዩነቶች አሉን። ልዩነት የምንፈታው ደግሞ በጉልበት/በጠብመንጃ ነው። ከዚህ የተለየ አማራጭ ሲጀመር ትልቅ ዜና ነው።

ሀገራችንን “እንወዳለን” የሚሉ በውጭ ያሉ የተለያዩ “ሚዲያዎች” ይህ ዜና አልሆን ብሏቸው ስንብቷል። እንወዳታለን የሚሉትን ሀገር እየነከሱ ፍቅር አልገባ ብሎኛል።

እነዚሁ አካላት አሁን ደግሞ መግባባት የተደረስባቸው ሳይሆኑ፣ ቀድሞም የልዩነት ነጥብ የነበሩ ጉዳዮች ልዩነት ሆን ብለው ዜና እና ሰበር ዜና እያደረጉት ይገኛል። ጎበዝ በዚህ ዘመን ዜና ምንድነው? ብሎ ጎግል መጠየቅ እንዴት ይከብዳል?

ጎበዝ ቀድሞም ለምክክር የተቀመጥነው ልዩነት ስላለን ነው። ይህ ዜና አይሆንም። ዜና የሚሆነው፣ ልዩነት ያላቸው ሃሳቦች በስለጠነ መንገድ ውይይት ማድረግ መቻሉ ነው። ከታገሳችሁ የስነስርዓት ጉዳይ ሆኖብን እንጂ ዜና የሚሆኑ፣ እንደ ጉድ የሚተረኩ ጉዳዮች አሉ።

ጨዋነት ይዞን፣ ሀገር ብለን ዋጥ ያደረግነው፣ የምክክር ሂደቶች አሉ። ዱብ እዳ አይደሉም። ግርምት የሚፈጥሩ፣ ዋው! የሚያስብሉ ናቸው። ጥሩ ዜና መዋል ካለ በቅጡ ይሰንዳቸዋል።

በነገራችሁ ላይ ሁሉም እንቅስቃሴ በኮምሽኑ ሪከርድ የሚደረግ ነው። ያልሆነ ሆነ ብሎ ተረት ተረት ማቅረብ ወደፊትም አይቻልም። ይህ ታሪክ ነው። ጎበዝ ዜናውን በአግባቡ ካልሰራችሁ የታሪኩ አካል አትሆኑም።

አትክልተኛው፣ የደሴቲቱ ነዋሪ!!
ከምክክር ደጃፍ!!


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: