የቻይናው ፈጣን ባቡር አዲስ የዓለም ሪኮርድ አስመዘገበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዓለምን የኢንጂነሪንግ እና የቴክኖሎጂ አቅጣጫ በግንባር ቀደምትነት እየመራች የምትገኘው ቻይና በፈጣን ባቡር ዘርፍ አዲስ የዓለም ሪኮርድ አስመዘገበች።

ይህ ዘመናዊና እጅግ ፈጣን የሆነው አዲሱ የቻይና ባቡር በሰአት ከ800 ኪሎሜትር በላይ እንደሚጓዝ ተነግሯል።

በሰዓት 800 ኪሎሜትር ማለት ከተራ የባቡር ፍጥነት አልፎ ከአብዛኞቹ የንግድ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ፍጥነት ጋር እኩል የሚያሰልፈው የቴክኖሎጂ ተአምር ነው።

በዚህም ግዙፍ የቴክኖሎጂ ምጥቀቷን እና የሳይንስ አቅሟን ለመላው ዓለም ዳግም አሳይታለች።

ይህ ስኬት በቀላሉ የፍጥነት መጨመር ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በኢንጂነሪግ ዘርፍ ላይ የደረሰችበትን ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ አሳይታለች።

ቻይና እጅግ ውስብስብ የሆኑ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም ይህንን እጅግ ዘመናዊ ባቡር እውን አድርጋለች።

ባቡሩ በከፍተኛ ፍጥነት ሲጓዝ የሚያጋጥመውን የነፋስ ግፊት ለመቀነስ የተጠቀመችው የላቀ የኤሮዳይናሚክስ ዲዛይን እና ግጭትን የሚቀንሰው የኤሌክትሮማግኔቲክ ሌቪቴሽን ቴክኖሎጂ የቻይናን ከፍተኛ የፊዚክስና ኢንጂነሪንግ ብቃት አስመስክሯል።

ባቡሩ በሴኮንድ ሚሊዮን መረጃዎችን በመተንተን ሊከሰቱ የሚችሉ የቴክኒክ ችግሮች አስቀድሞ በመለየት ፍጹም አስተማማኝ ደህንነትን ያረጋግጣል።

ቻይና በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ የበላይነትን ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#ChinaBulletTrain #TechNews #HighSpeedRail #EthiopiaTech #WorldRecord #BreakingNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: