#Ethiopia | በአዲስ አበባ በያዝነው ዓመት ከተመዘገቡ የትራፊክ ደንብ መጣሶች መካከል ቁጥራቸው ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107 ነጥብ 8 ታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ በቀረቡበት ወቅት አስታውቀዋል።
ከተመዘገቡት ጥሰቶች ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀይ መብራት ጥሰው የማለፍ ድርጊቶች እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ውስጥ ከ900 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚንቀሳቀሱ ተመልክቷል።
ዋና ኢንስፔክተሩ የትራፊክ ደንብን አለማክበር ለሰው ሕይወት ማለፍና ለንብረት ውድመት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን አሳስበዋል።
ሆኖም በተደረገው ጥብቅ ቁጥጥርና የቅጣት አፈጻጸም ምክንያት አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ውጤት እየታየ ይገኛል።
በዚህም መሠረት በ2017 ዓመተ ምህረት 411 የነበረው የሞት አደጋ በ2018 ዓመተ ምህረት ወደ 382 ዝቅ ብሏል።
እንዲሁም የከባድ አደጋዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 985 ወደ 1 ሺህ 865 በመቀነስ የ120 አደጋዎች ቅናሽ አሳይቷል።
በሌላ በኩል ግን ቀላል አደጋዎች ከ115 ወደ 735 ያደጉ ሲሆን የንብረት ጉዳቶች ደግሞ ከ34 ሺህ 84 ወደ 34 ሺህ 702 ከፍ ብለዋል።
በመጨረሻም አሽከርካሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ሕግን በማክበር ማሽከርከር እንዳለባቸውና የሰዎችን ሕይወትና ንብረት ከውድመት እንዲታደጉ ጥሪ ተ አስተላልፏል።
#traffic #addisababatraffic #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen








No comments yet.