ኤምባሲው በቤት ኪራይ ዕዳ ምክንያት ተዘጋ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኬንያ ናይሮቢ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ መንግሥት የነበረበትን የአራት ወራት የቤት ኪራይ ክፍያ መፈጸም ባለመቻሉ ምክንያት መዘጋቱ ተገለጸ።

ይህ በመሆኑ ምክንያት በኬንያ የሚኖሩ በርካታ የደቡብ ሱዳን ዜጎች ያገኙት የነበረውን የቆንስላና የጉዞ ሰነዶች ማግኘት አልቻሉም ተብሏል።

የኤምባሲው ሰራተኞች የህንፃው አከራይ በኪራይ ዕዳው ምክንያት ኤምባሲውን በመቆለፋቸው ተቋሙ አገልግሎት መስጠት አቁሟል ብለዋለ።

የደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ ኤምባሲው ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጻል።

የደቡብ ሱዳን የሲቪል ማህበራት ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ኤድመንድ ያካኒ ድርጊቱን አሳዛኝ እና የሀገሪቱን ዲፕሎማሲያዊ ገጽታ የሚያጎድፍ ሲሉ ገልጸውታል።

ያካኒ አክለውም የደቡብ ሱዳን መንግሥት በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ላይ ያለውን ስትራቴጂያዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ለውጭ ሀገር ኤምባሲዎች የበጀት ክፍያ ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።

ደቡብ ሱዳን ከባድ ኢኮኖሚያዊ ውጥረት ውስጥ በመሆኗ ምክንያት በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኤምባሲዎቿ እና ዲፕሎማቶቿ የደሞዝ እና የተቋማት የሥራ ማስኬጃ በጀት እጥረት እንዳጋጠማት ተሰምቷል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Kenya #SouthSudan
#Embassy #rentpayments


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2